teddy love




የእለቱ ጥቅስ

«በጸሎትና በጾም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም» ማርቆስ 9፡29

ማስታወቂያ
hyawEwnet.jpg
Site Last Updated:-Monday 27 December 2010
ልዩ ልዩ ትምህርቶች
ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው!

St.Marry1.JPG                      St.Marry.JPG

ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ
በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው!

             መዝ.86፥3

 

በመ/ር መንግስተ አብ ፡አበጋዝ
 
የሶርያው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም የምስጋና መጽሐፉ ‹‹ነቢያት ድንቅ ድንቅ ነገርን ተናገሩልሽ›› በማለት ስለ ወላዲተ አምላክ የተሰጡ ምስክርነቶች ድንቆች መሆናቸውን መስክሯል፡፡ ከዛሬ 3000 ዓመት ገደማ ቀደም ብሎም ነቢየ እግዚብሔር ዳዊት ‹‹ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ኦ ሀገረ እግዚአብሔር፤ የእግዚአብሔር ከተማ /ሀገር/ ሆይ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው፡፡›› /መዝ.86፥3/ በማለት አመስግኗታል፡፡ እነዚህ በተለያየ የዘመን ርቀት ውስጥ የኖሩ የነቢዩ ዳዊትና የቅዱስ ኤፍሬም ምስጋና ምን ይደንቅ?!
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
ቅዱሳን መላእክት
ታኅሳስ 19 ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል በዓል በቤተክርስቲያናችን በማኅሌት፣ በቅዳሴና በሌሎች መንፈሳዊ መርሐ ግብራት ይከበራል፡፡ ይህንን ምክንያት አድርገን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ስለቅዱሳን መላእክት ያስተማሩትን ትምህርት አቅርበናል፡፡

 
መድኅን ተወልዶላችኋል

መድኅን ማለት አዳኝ ወይም መድኃኒት ማለት ሲሆን ይህም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ቤዛ ስለሆነ ቀደም ብለው ነቢያት ትንቢት ሲናገሩለት ቆይተው ነበር ከዚህም የተነሳ መድኅን የተባለው ቃል ለረጅም ዘመናት በተስፋ ሲጠበቅ የኖረ ስለነበረ በተፈጸመ ጊዜ ሁሉ ነገር ታደሰ፡፡ የዳዊት ከተማ በነበረችው በቤተልሔም የዘመኑ ፍጻሜ ደረሶ መድኃኒትነቱ በነቢያት የተነገረለት መድኅን ክርስቶስ በመወለዱ ከመርገም በታች ወድቆ ይኖር የነበረውም የሰው ልጅ ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋገረ፡፡ በኃጢአት አርጅቶ የነበረው አሮጌው ዓለም መልኩን ለውጦ አዲስ ሆነ፡፡ ከዚህ በፊት ተደረጎ የማያውቀውና ወደፊትም ሊደረግ የማይታሰበው ረቂት ምሥጢር በመገለጹ የሰማይ መላእክትና በሌሊት መንጋቸውን አሰማርተው ይጠብቁ የነበሩት እረኞች «ሰላም በምድር እርቅም ለሰው ልጅ ይሁን» እያሉ በኅብረት ዘመሩ፡፡ ለሰው ልጆች ታላቅ ደስታና ሰላም ተፈጽሟልና፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
ስለምን አትጠግኗቸውም?
/2ነገ.12-8/

በአምባቸው ጸጋዬ

ኢዮአስ የይሁዳ ስምንተኛው ንጉሥ ነው፡፡ አባቱ ንጉሡ አካዝያስ ሲሆን እናቱ የቤርሳቤህ ከተማ ተወላጅ የነበረችው ሳብያ ናት፡፡ በንግሥና ዘመኑ ምንም እንኳ የኮረብታ ማምለኪያ ሥፍራዎች ጨርሰው ባይጠፉም፤ መቅደሰ እግዚአብሔር ፈርሶ ነበርና በንግሥና ዘመኑ መጀመሪያ ከፈጸማቸው በጎ ምግባራት መካከል መቅደሱ እንዲታደስ ማዘዙ ነበር፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ...
 
አስተርእዮ

«እግዚአብሔር እግዚእ አስተርአየ ለነ = በምልአቱ ያለ እግዚአብሔር በሥጋ ተገለጠልን፡፡» መዝ.117.27

በትምህርተ ወንጌል = ሃይማኖት
በሃይማኖት =  ጥምቀት = ዳግም ልደት፣
በጥምቀት =  ልጅነት፣ስርየተ ኀጢአት፣ተስፋ መንግሥተ ሰማያት፣ ገቢረ ተአምራት ወመንክራት፣ለሚገኝባትና ለሚሰጥባት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሕግ፣ ሥርዐት፣ መለያ፣ ውበት፣ ሽልማቷ ነው፡፡ ማቴ.14.17፣1ኛ ቆሮ.14.4ዐ፣ዕብ.9.1- . . እንዲህ በመሆኑም ከጥር ዐሥር ቀን ወይም ከጥምቀት ገሃድ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ዐቢይ ጾም መያዣ ቅበላው ድረስ ያሉት ሳምንታት፣ወራት ልዩ ልዩ የምስጢረ አድኅኖት ስያሜዎች አሏቸው፡፡ እነዚህም

ተጨማሪ ያንብቡ...
 
<< መጀመሪያ < ወደኋላ 1 2 3 4 5 ወደፊት > መጨረሻ >>

ውጤቶች 19 - 27 ከ 45












 

 Picture of Virgin Saint Mary, the Mother of God

 

Text Box: Text Box:




2

2

3

4

5

6

Text Box: HOW TO CHALLENGE LIFE?  Text Box: Secondary Story Headline Text Box: Text Box: Text Box: Newsletter Date Text Box: Text Box: ADDIS HIWOT  Text Box: Volume 1, Issue 1

    


 i     love you marry              AM

Teddy Abebe

 

This free website was made using Yola.

No HTML skills required. Build your website in minutes.

Go to www.yola.com and sign up today!

Make a free website with Yola